የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይፋዊ ዌብሳይት

ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን)

ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) በአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን የሚንቀሳቀስ በ1970ዎቹ መጨረሻ የተመሠረተ ታጣቂ ድርጅት ነው፡፡ ኤችኪውኤን በዩናይትድ ስቴትስ እና በአፍጋኒስታን የጥምር ጦር አባላት ላይ በርካታ ከፍተኛ ጥቃቶች እና እገታ ፈጽሟል፡፡ በሰኔ 2004 ዓ.ም. በኮስት፣ አፍጋኒሰታን የአሜሪካ የጦር ካምፕ ላይ የተፈጸመው የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ጥቃት ሁለት የአሜሪካ ወታደሮችን ሲገድል ከ100 በላይ የሆኑትን ደግሞ አቁስሏል፡፡ የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት በግንቦት 2009 ዓ.ም. ተፈጽሞ ከ150 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገው በጭነት ተሽከርካሪ ላይ ለተጠመደ የቦምብ ፍንዳታ ፈጻሚው ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) ነው ብለዋል፡፡ ሃቃኒ ኔትወርክ ከ100 በላይ ሰዎች የገደለው፣ በካቡል ለተፈጸመው በአምቡላንስ የተጠመደ ቦምብ ኃላፊነቱን ይወስዳል ተብሎ ይታመናል፡፡ እንዲሁም የአፍጋኒስታን ባለሥልጣናት በጥር 2010 ለተፈጸመው እና በካቡል በሚገኘው ዓለም ዓቀፍ ሆቴል ላይ ተፈጽሞ 22 ሰዎችን የገደለው ጥቃት ፈጻሚ ሃቃኒ ኔትወርክ ነው ብለዋል፡፡

በመስከረም 09 ቀን 2005 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ብሎ በመጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃቃኒ ኔትወርክ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃቃኒ ኔትወርክ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሃቃኒ ኔትወርክ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሃቃኒ ኔትወርክ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

SUBMIT A TIP

Do Your Part. Secure a Safer World.

There are many ways to submit information to Rewards for Justice.

You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.

Please visit our Tor-based tips-reporting channel at: he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

መረጃ ይስጡ

የበኩልዎን ያድርጉ

መረጃ ለማቅረብ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡

ከተለያዩ ፕላትፎርሞች ሊመርጡ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ የእርስዎን መረጃ በውጤታማነት ለማካሄድ እንዲችሉ፣ የሚሰጡትን መረጃ በተቻለ መጠን እጥር፣ ምጥን ባለ መልኩ እንዲያቀርቡ እንጠይቅዎታለን፤ እንዲሁም ስምዎን ፣ የሚገኙበትን ቦታ፣ የሚመርጡትን ቋንቋ እና እንደ ፎቶግራፍ፣ ቪድዮ እና ሰነዶች ያሉ የእርስዎን መረጃዎች የሚደግፉ ማስረጃዎች አፕሎድ እንዲያደርጉ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡ የወሮታ ለፍትሕ ወኪልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኝዎታል፤ እባክዎን በትዕግስት ይጠብቁን፤ ወሮታ ለፍተሕ እያንዳንዱን መረጃ ያነብባል፡፡

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

Skip to content